News News
Minimize Maximize
« Back

ከተሞች የፈጣን ልማትና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕከላት እንዲሆኑ ከተፈለገ የባለድርሻ አካላት ርብርብና ተሳትፎ ከፍተኛ መሆን ይኖርበታል ተባለ

ከተሞች የፈጣን ልማትና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕከላት እንዲሆኑ ከተፈለገ የባለድርሻ አካላት ርብርብና ተሳትፎ ከፍተኛ መሆን ይኖርበታል ሲሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አምባቸው መኮነን ተናገሩ፡፡ መንግስት የከተሞቻችንን እድገት ለማፋጠን የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ፕሮግራሞችን ነድፎ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለዚህ ውጤት መሳካት ደግሞ የመንግስትና የህዝብ ክንፍ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ተሳተፎ ወሳን ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የዘርፉ ሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዋና ዋና ግቦች እና የእሰካሁኑ አፈጻጸም እንዲሁም የ2010 በጀት ዓመት እቅድ ለዘርፉ የህዝብ ክንፍና ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በውይይቱም የመደረኩ ተሳታፊዎች በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በማመስገን አሉ ያሏቸውን ችግሮች በማንሳት እና በቀጣይ ከዚህ የበለጠ እንዴት አብሮ መስራት እንደሚቻል ሃሳብ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ውይይቱን ሲመሩ የነበሩት ሚንስትሮች በበኩላቸው አገራችን በ2017 የመካከለኛ ደረጃ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመድረስ የሚያስችላት ራዕይ ቀርጻ እውን ለማድረግ ትገኛለች በዚህም የከተማ ልማት ዘርፉ ትልቁን ድርሻ ስለሚይዝ የዘርፉ የህዝብ ክንፍ፣ አመራርና ባለድርሻ አካላት በተገቢው መንገድ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡