News News
Minimize Maximize
« Back

በ2017 ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት ግንቦት 18 ቀን 2008 . በአዲስ አበባ ከተማ ስምምነት አካሂደዋል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ገብረ ጊዮርጊስ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ብዙአለም አድማሱ እና ከኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆን ኮዋን ናቸው፡፡ የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት የጋራ ትብብራቸውን በማጠናከር በአዳዲስ ከተሞች ምስረታ፣ በከተሞች ልማት፣ በከተማ መሬት ልማትና በቤቶች ዘርፍ፣ በሰው ሃይል ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጾል፡፡ ከዚህ ቀደም በሚኒስቴር ደረጃ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከኮሪያ የመሬት፣መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር መፈራራማቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ስምምነቱን ተጨባጭ ለማድረግና ወደትግበራ ለመግባት በቢሮ ደረጃ ስምምነቱ ማካሄድ አስፈልጓል ብለዋል፡፡ የኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆን ኮዋን በበኩላቸው በከተማ ልማት ዘርፍ ተሞክሮቸውን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ስምምነቱ በከተማ ልማት፣ በመሰረተ ልማት ዘርፍና በሌሎች ዘርፎች አስተወጽኦ እንዲናደርግ ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡ በሚኒስቴሩ የሚኒስትሩ አማካሪ ቡድን /ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይትባረክ መንግስቴ ቀደም ሲል ከደቡብ ኮሪያ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች እንደ ሀገር የተደረጉ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ በከተማ ዘርፍ ያላቸውን ጥሩ ተሞክሮ ለማግኘት የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ ኃላፊው ስምምነቶቹ በዋነኛነት የሚያተኩሩት በከተማ ፕላንና በከተሞች ማስፋፋት ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥተው ሊሰራባቸው የሚገቡ ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ነው፡፡ እንደ ሀገር ካለው ፈጣን እድገት ጋር ተያይዞ ሰፊ የሆነ የመሬት ፍላጎት አለ ያሉት ኃላፊው ስምምነቱ መሬት በአግባቡ እንዴት እንደሚለማና ለልማት እንደሚቀርብ ተሞክሮ ለመውሰድ ያግዘናል ብለዋል፡፡ በቤት ልማት ላይ ያላቸውን ሰፊ ልምድ በመውሰድ ከግንባታውም በዘለለ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራውን የቤት ልማት አስተዳደር ስራ እንዴት መመራት እንዳለበት እውቀት ለመውሰድ ስምምነቱ እንደሚያግዛቸው የተናሩት አቶ ይትባረክ በእነዚህ መስኮች ላይ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በመምጣት ለባለሙያዎቻችን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይም ባለሙያዎቻችን ወደውጭ በመሄድ ስልጠና የሚያገኙበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል፡፡