News News
Minimize Maximize
« Back

በከፍተኛ ፍጥነት በህዝብ ቁጥር እያደጉ ያሉ ከተሞቻችንን እንዴት ከአየር ብክለት መከላከል እንችላለን?

የከተሞች በፍጥነት ማደግና መስፋፋት ብዙ ህዝብ ከሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎችና አጎራባች ከተሞች የሚያደርገዉ ፍልሰት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡ እነዚህ በፍልሰት የመጡ ነዋሪዎች የከተማዉ መሰረተ ልማት መሸከም ከሚችለዉ በላይ ስለሚሆኑና የተመቻቸ መኖሪያና የስራ ቦታ የሌላቸዉ በመሆኑ መንግስት ብዙም ትኩረት አይሰጠዉም በማለት በሚያስቡት በዉሀ አካላት ዳርቻ አካባቢ በመስፈር የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔዎች ያካሄዳሉ፡፡ የዉሃ ምንጮች በሰዉ ልጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ጫና ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠናቸዉ እየቀነሰና እየጠፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዉሀ አካላቶች ከሚፈለገዉ በላይ ለተለያዩ አገልግሎቶች መጠቀም፣ ከኢንዱስትሪ የሚወጡ ኬሚካሎች ወደ ወንዝ መልቀቅና የዉሀ ምንጮችን መበከል፣ በሀይቅ ምንጭ አካባቢ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን አፈር ወደ ሀይቁ እንዲገባና በደለል እንዲሞላ በማድረግ፣ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ዉሀ አካላቶች በመልቀቅ የወንዞች የተፈጥሮ ፍሰት እንዲስተጓጎልና እንዲቆራረጥ በማድረግ፣ በወንዝ ዳርቻ አካባቢ ለወንዞች መጠበቂያነት የተተከሉትና በተፈጥሮ የበቀሉትን ደኖች በመቁረጥ የዉሀ ስርገት እንዲቀንስ፤የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት እንዲባባስ በማድረግ የዉሀ ምንጮች እንዲጠፉ እያደረገ በመሆኑ ምክንያት በወንዝና ወንዝ ዳርቻዎች አካባቢ በሚገኙ ሰነፍጥረታት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል (World Bank, 2007)::

ጠቀሜታዎች ጤናማ የዉሃ አካላትና ዳርቻዎች ለዱር እንስሳትና እጽዋቶች በተለይም እንስሳቶች የሚመቻቸውን አካባቢዎች ፍለጋ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ መንገድ የሚሆኑ ከመሆናቸዉም በተጨማሪ ለመጥፋት የተቃረቡ ዝርያዎች በአየር ንብረት ለውጥ ሂደት ውስጥ ሊታደጉ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዉሀ አካላቶችና በዉሀ አካላት ዳርቻዎች አማካኝነት የተሻሻለ የመኖሪያ አካባቢ በማገናኘት ለብዝሃ ሕይወት ጥበቃ እና በከተሞች ያሉት የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶችን ትስስር ለመፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም በዉሃ አካላትና ዳርቻ ያሉ ተፈጥሮአዊ አካባቢዎችን ወደነበሩበት ሁኔታ የመመለስ ሂደት የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትላቸው አደጋዎች በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም የዉሃና የዉሃ ዳርቻ ቦታዎች ለዋና፣ ለትራንስፖርት፣ ለሰርግና ለአእምሮ ማሳረፊያ ቦታነት፣ ለቱሪስት መስህብነት፣ አንዲሁም ለከተሞች ተጨማሪ ዉበት በማጎናጸፍ የሚሰጡት ጠቀሜታ በጣም ከፍተኛ ነዉ፡

የተያያዙ ችግሮች መንስዔዎች ጥቂቶቹ በሀገራችን የከተሞች የወንዝ ዳርቻና የዉሀ አካላት ብክለት መንስኤዎች የተለያዩ ሲሆኑ ኢንዱስትሪ፣ የማዘጋጃ ቤት ቆሻሻ፣ የጤና ተቋማት ቆሻሻ፣ ከተለያዩ ጋራዦችና ነዳጅ ማደያዎች የሚወጡ ቆሻሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ቦታዎች ለመኪና እጥበት መጠቀም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡

ከኢንዱስትሪ የሚወጣ ቆሻሻ

በአጠቃላይ ኢንዱስትሪዎች ዋና የዉሀ አካላት የብክለት መንስኤዎች ሲሆኑ ከሚለቁዋቸዉ በካዮች መካከል ዘይት፣ ፀረ-ተባይ መድሀኒት፣ ናይትሬት፣ ፎስፌት፣ ሰልፌት፣ ክሎራይድ፣ አሲድ እና የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ በካይ ንጥረ ነገሮች ወንዞችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚበክሉ ሲሆን በተበከለ ዉሀ የሚለማ የወንዝ ዳርቻ ግብርና በአልሚዉና በተመጋቢዉ ህብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሲሆን

በተመሳሳይ ሁኔታም በወንዝና ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚኖሩት ስነ-ፍጥረታት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅእኖ አቃቄ ወንዝ ቀበና ወንዝ ያሳድራሉ፡፡

ከዚህ ዉስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ከፋብሪካ የሚለቀቅ ፍሳሽ ቆሻሻና በወንዝ ዳርቻ አካባቢ የሚከማች የፋብሪካ ተረፈ ምርት ለአብነት ማየት ይቻላል፡፡

ከተለያዩ ጋራዦችና ነዳጅ ማደያዎች የሚወጡ ቆሻሻዎች

በሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች በርካታ ነዳጅ ማደያዎችና ጋራዦች የሚገኙ ሲሆን ከነዚሁ ተቋማት የሚወጣ የተቃጠለ ዘይትና በካይ ንጥረ ነገሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በጎርፍ እየታጠበ ወደ ወንዝና የዉሀ አካላት ዉስጥ በመግባት ዉሃዉን እየበከለ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ላይ የሚካሄደዉ የግብርና ምርት አምራችና ተመጋቢ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ በዉሀ ዉስጥና በወንዝ ዳርቻ ላይ በሚኖሩት ስነ-ህይወት ላይ የሚያስከትለዉ አሉታዊ ተፅእኖ ከፍተኛ አንደሆነ መገንዘብ ይቻላል

መፈትሄዎች

የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማጠናከር የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን የተሳትፎ አግባብ ለማሳደግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ በተዘጋጀው ማንዋል መሰረት ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር፣ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላቱ ፋይናንስ፣ ጉልበት፣ ግብዓት በማቅረብና በመሳሰሉት ላይ እንዲሳተፍ በማድረግ፡፡

  • የዉሃ አካላቶችንና ዳርቻ ቦታዎችን ንጹህና አረንጓዴ በማድረግ ዉብና ማራኪ አካባቢ እንዲፈጠር ማድረግ፤
  • የህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላቶችን ተሳትፎ በማጎልበት የዉሃ አካላቶች ከብክለት የሚጠበቁበት ሁኔታ ማመቻቸት፤
  • በዉሃ አካላትና ዳርቻዎች ላይ የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊና ሰዉ ሰራሽ ችግሮችን በመከላከል የብዝሀ ህይወት ሀብታችንን እንዲጠበቁ ማድረግ፤
  • የከተማ ዉሃ አካላትና ዳርቻ ቦታዎች ለዱር እንስሳትና አእዋፍ መተላለፍያ ቀጠናነት (ኮሪደርነት) እንዲያገለግሉ ማድረግ፤
  • የከተማ የዉሃ አካላት ዳርቻ ቦታዎች አያያዝ በማሻሻል የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ እንዲጠበቅ ማድረግ፤
  • የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋን እንዲቀንስ ለማድረግ፤ በዉሃ አካላቶችና ዳርቻ ቦታዎችበስታንዳረዱ መሰረት በማልማት ለዜጎች የስራ አድል የሚፈጠርበት ሁኔታ ማመቻቸት፡፡

በአጠቃላይ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የሚፈጠሩ ችግሮችን እልባት ለመስጠት የሁሉም ባለድርሻ አካለት ርብርብና ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ልማቱ ሊሳካ የሚችለው በመንግስት ጥረት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና የመንግስት አጋር በመሆን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂዱት የለውጥ እንቅስቃሴ ነው፡፡ማጠቃለያው ችግሮች ፈጣሪውም መፍትሄውም ሰው ነው፡፡

ምንጭ፡-የከተሞች የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ቢሮ