News News
Minimize Maximize
« Back

በከተሞች የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ሰፈርን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ መሰራት ያስፈልጋል

 በከተሞች የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ሰፈርን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ መሰራት ያስፈልጋል

 

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በዘርፉ ያለውን የህዝቡና የባለሚና ተሳትፎን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ካላፈው አፈጻጸም እጅግ የተሻለ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ ቀልጣፋና ብቃት ያለው አገልግሎት ለማቅረብና በሁለንተናዊ የከተማ ልማት ስራዎች እምርታ ሊያመጡ የሚያስችሉ አጀንዳዎችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ በዚህም መሰረት በተመረጡ የከተማ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ህዝባዊ ውይይት በማካሄድ ንቅናቄ መፍጠር ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳይ ተደርጓ ተወስዷል፡፡ በከተማ ስራ የህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑና የከተማ ልማት ስራዎችን ምልዓተ ህዝቡ በጥልቀት ተገንዝቦ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባትና የራሱን የጎላ ድርሻ በመወጣት ህዝቡን እያማረሩ የሚገኙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ህዝባዊ የንቅናቄ ውይይቶች ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴሩ በተመረጡ የህዝብ ንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ ከ9ኙ ክልሎችና ከ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዳራሽ ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ደምሴ ሽቶ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የከተማ አጀንዳዎች በህዝብ ንቅናቄ ለማሳካት በሁሉም ክልሎች በተለያየ ደረጃ የሚገኝ የህዝብ ንቅናቄ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ የህዝብ ንቅናቄ አጀንዳዎችን በዋና ዋና የከተማ አጀንዳዎች ዙሪያ ለመቅረጽና በየክልሉ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲሄድ ለማስቻል ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ ተቀራራቢ በሆነ ሁኔታ መሄድ ይችላል የሚችለበትን መንገድ ለመደገፍ የሚያስችል ሰነዶች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡ ሰነዶቹ በተለያዩ ጊዜ ውይይት ተካሂዶባቸውና ጸድቀው ወደ ስራ ተገብቷል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በዚህም መሰረት የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ከተሞች ለመማርና በተለያየ ምክንያት ወደ ንቅናቄ ስራ ያልገቡ ከተሞችም ልምድ እንዲወስዱ ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በፌደራል ደረጃ በዋና ዋና አጀንዳዎቹ ዙሪያ ንቅናቄ በመፍጠር ወደ ስራ ለመግባት በተለዩት 3 አጀንዳዎች መሰረት በከተማ ፕላን እና በጽዳትና አረንጓዴ ልማት የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች መዘጋጀታቸውን ያስታወሱት ሚኒስትር ዲኤታው በተለያዩ ምክንያቶች የመሬት ልማትና ማኔጅመንት አጀንዳ ሊዘገይ እንደቻለ አስረድተዋል፡፡ የህዝብ ንቅናቄዎቹ በክልሎች፣ በከተሞች፣ በክፍለ ከተሞችና በሰፈር ደረጃ እንደሚሰሩና በዋናነት ንቅናቄው የተለያዩ የሰፈር እንቅስቀሴዎችን መሰረት እንደሚኖርበት የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው በሰፈር ደረጃ ምን መስራት እንዳለበት በንቅናቄ ሰነዶች በዝርዝር እንደተብራሩ አስረድተዋል፡፡ አንድ ሰፈር ውስጥ ያሉ ጉዳዮች በየሰፈሩ የሚፈቱ ከሆነ በአካባቢው የሚገኙ ችግሮች በሙሉ ይፈታሉ ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ‹‹እያንዳንዱ ሰፈሩን ካስተካከለ ከተማው በሙሉ ይስተካከላል›› በሚል ሰፈርን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ መስራት ያስፈልጋል፡፡ እነዘህ ሰፈሮች ለውጥ አምጥተው የሚሄዱ ከሆነ ህዝቡ ባለቤት ሆኖ እንዲመራ የማድረግና ለዚህ ግልጽ አሰራር የመፍጠር ጉዳይ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ውይይት ይካሄድባቸው ተብለው የተለዩት ዋና ዋና የንቅናቄ አጀንዳዎች የከተሞች የምግብ ዋስትናና የስራ እድል ፈጠራ፣ የከተሞች ልማታዊ መልካም አስተዳደር፣ የከተማ ፕላን፣መሬት ልማትና ማኔጅመንት፣ የከተማ የተቀናጀ መሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር እና የከተሞች ጽዳትና አረንጓዴ ልማት ናቸው፡፡ ለሁለት ቀናት በቆየው ስልጠና ከላይ የተዘረዘሩት የንቅናቄ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዷባቸዋል፡፡