News News
Minimize Maximize
« Back

ስምምነት

 ሚኒስቴሩና የኮሪያ መሬትና ቤቶች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

 

በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት ግንቦት 18 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ስምምነት አካሂደዋል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ገብረ ጊዮርጊስ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ብዙአለም አድማሱ እና ከኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆን ዶ ኮዋን ናቸው፡፡ የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት የጋራ ትብብራቸውን በማጠናከር በአዳዲስ ከተሞች ምስረታ፣ በከተሞች ልማት፣ በከተማ መሬት ልማትና በቤቶች ዘርፍ፣ በሰው ሃይል ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጾል፡፡ ከዚህ ቀደም በሚኒስቴር ደረጃ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከኮሪያ የመሬት፣መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር መፈራራማቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ስምምነቱን ተጨባጭ ለማድረግና ወደትግበራ ለመግባት በቢሮ ደረጃ ስምምነቱ ማካሄድ አስፈልጓል ብለዋል፡፡ የኮሪያ የመሬትና ቤቶችና ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆን ዶ ኮዋን በበኩላቸው በከተማ ልማት ዘርፍ ተሞክሮቸውን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ስምምነቱ በከተማ ልማት፣ በመሰረተ ልማት ዘርፍና በሌሎች ዘርፎች አስተወጽኦ እንዲናደርግ ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡ በሚኒስቴሩ የሚኒስትሩ አማካሪ ቡድን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይትባረክ መንግስቴ ቀደም ሲል ከደቡብ ኮሪያ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች እንደ ሀገር የተደረጉ ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ በከተማ ዘርፍ ያላቸውን ጥሩ ተሞክሮ ለማግኘት የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ ኃላፊው ስምምነቶቹ በዋነኛነት የሚያተኩሩት በከተማ ፕላንና በከተሞች ማስፋፋት ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥተው ሊሰራባቸው የሚገቡ ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ነው፡፡ እንደ ሀገር ካለው ፈጣን እድገት ጋር ተያይዞ ሰፊ የሆነ የመሬት ፍላጎት አለ ያሉት ኃላፊው ስምምነቱ መሬት በአግባቡ እንዴት እንደሚለማና ለልማት እንደሚቀርብ ተሞክሮ ለመውሰድ ያግዘናል ብለዋል፡፡ በቤት ልማት ላይ ያላቸውን ሰፊ ልምድ በመውሰድ ከግንባታውም በዘለለ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራውን የቤት ልማት አስተዳደር ስራ እንዴት መመራት እንዳለበት እውቀት ለመውሰድ ስምምነቱ እንደሚያግዛቸው የተናሩት አቶ ይትባረክ በእነዚህ መስኮች ላይ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በመምጣት ለባለሙያዎቻችን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይም ባለሙያዎቻችን ወደውጭ በመሄድ ስልጠና የሚያገኙበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል፡፡

 ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ፣ጥራትና ስታንዳርድ እንዲገነቡ ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

 

ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ፣ጥራትና ስታንዳርድ እንዲገነቡ ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራዝ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባተ ስጦታው ጥሪ አቀረቡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ የ2007 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምና የ2008 ዓ.ም እቅድ ላይ ከስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ጋር በኢትየጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ከመስከረም 5-6 ቀን 2008 ዓ.ም በተካሄደው ዉይይት ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባው ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ፣ጥራትና ስታንዳርድ እንዲገነቡ ማድረግ አለብን፡፡ ለዚህም ስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና አስፈጻሚ አካላት(ባለቤቶች) በባለቤትነት ስሜትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

 

ለግንባታ መጎተት የሚጠቀሱ መሰረታዊ ችግሮች የግብዓት አቅርቦት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የፕሮጀክት ማጅመንት ችግር፣ የዲዛይን ችግርና መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት ናቸው የግብዓት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው በተቻለ መጠን ችግሩን ለመቅረፍ ግብዓቶችን ከሀገር ዉስጥ እንዲገቡ እያደረግን ነው፡፡ ችግሩንም ለመቅረፍ ግንባታ ከመጀመራቸው በፊት አስቀድሞ ግብዓቶችን ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ብቃትን መሰረት ያደረገ አሰራርን በመከተል የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ስራ ተቋራጮች መለየትና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ከንቲባው የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ተጨማሪ ስራ ለመስጠት እንደተዘጋጁ ተናግረዋል፡፡

በዉይይቱም ላይ የኢንተርፕራይዙ የ2007 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ዉይይት ተካሂዷበታል፡፡ በስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና ባለቤቶች (አስፈጻሚ አካላት) የታዩ ችግሮች ተነስተው ዉይት ተካሂዷበታል፡፡

በስራ ተቋራጮች የታዩ ችግሮች መካከል ግብዓትን በእቅድ ያለማቅረብና ያለመቀበል፣ የአቅም ዉስንነት፣ የባለቤትነት ስሜት መጎደል፣ የክፍያ ሰነድን አሟልቶ ያለመስጠት ይጠቀሳሉ፡፡ በአማካሪ በኩል የክፍያ ጥያቄ ማመላለስ፣ የስራ ትዕዛዝ በወቅቱ ያለመስጠት፣ ከጥራት ጋር መደራደር፣ የዲዛይን ለውጥን ቶሎ ብሎ ያለማድረስና ያለማጽደቅ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን ያለመደገፍ፣ ስራን በወቅቱ ያለመገምገም፣ የግንባታ ቁጥጥር መላላት የታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ 
በባለቤት በኩል አማካሪ ያዘጋጀውን ዲዛይን በፍጥነት ያለማጽደቅ፣ ስታንዳርድን ጠብቆ ያለመስራት፣ ግብዕትን በተመለከተ በእቅድ ያለመመራትና የስርጭት አድሏዊነት፣ ማህበራትን ቀድሞ ወደ ስራ ያለማስገባ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡

በ2007 ዓ.ም ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች በ2008 በጀት ዓመት እንዳያጋጥሙ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክንዴ ብዙነህ ናቸው፡፡ ከዲዛይን ጋር ተያይዞ የሚያጋጥመውን ችግር አማካሪዎችም ሆኑ ባለቤቶች በፍጥነት አስቸኳይ ምላሽ መስጠት ይገባቸዋል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ስራዎችንም በየወቅቱ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ጠቆመዋል፡፡

ለሁሉም አሰራሮች ስታንዳርዱን በመከተልና የጠራ እስፔሲፊኬሽን በማዘጋጀት እንዲሁም ዘመናዊ አሰራርን በመከተልና የተሻሉ ተሞክሮዎችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በ2007 ዓ.ም ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት ይገባል ተብሏል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በ2008 ዓ.ም ተቋማዊ አቅም በመፍጠር ጠንካራ የመልካም አስተዳደርና የልማት ሰራዊት በመገንባትና የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በዘርፉ የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ለመዋጋት እንደቆረጠ በመድረኩ ላይ ተገልጾል፡፡