News News
Minimize Maximize
« Back

ለ7ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም መሳካት የጎንደር ከተማ ህብረተሰብና ባለድረሻ አካላት ተሳትፎ የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

 


አዲስአበባ፡ ሚያዝያ 9 ቀን 2009 ዓ.ም

 

7ኛው አገር አቀፍ የከተሞች ፎረም ከሚያዝያ 21 እስከ 28 ቀን 2009 ዓ.ም መካሄዱን ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና አጋር አካላት ጋር እንዲሁም ከፌደራልና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ጋዜጠኞች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ሚያዝያ 2 ቀን 2009 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡በውይይት መድረኩም ከተለያዩ የሰሜን ጎንደር ዞን ወረዳዎች

የተወከሉ አመራሮችና የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በዓል መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው 7ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ከ200 ያላነሱ ከተሞች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስካሁንም ማለትም ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ወደ 215 ከተሞች መመዝገባቸው የታወቀ ሲሆን በቀጣይም በዓሉ እስከ ሚከበርበት ዕለት ድረስም ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል፡፡